Southwest Communications
swc79.bsky.social
Southwest Communications
@swc79.bsky.social
We are delivering you an update and reliable information about Southwest Ethiopia Peoples Regional state activities, news, and national & international issues
ግንባታው እየተገባደደ የሚገኘው የቦንጋ መናኸሪያ

ከ94 ሚሊዮን በላይ በኾነ ወጪ በክልሉ መንግሥት እየተከናወነ የሚገኘውን የመናኸሪያ ግንባታ ለማጠናቀቅ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ መመልከት ተችሏል።

የመናኸሪያው ምዕራፍ አንድ ግንባታ የአስፓልት ማንጠፍ ሥራ የቀረው ሲሆን ይህንንም ተግባር በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለአግልግሎት ለማብቃት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ
January 29, 2026 at 4:07 PM
''ሸኮ ጎዳ'' ከብት በወተትም ይሁን በሥጋ ጣዕምና ምርታቸዉ ከሀገረሰብ ከብቶች የተሻሉ በመሆናቸዉ ዝሪያቸዉን በማባዛቱ ረገድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

‎በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ፕሮግራም በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነዉ::

January 29, 2026 at 2:32 PM
የምድር መንትያ ተገኘች

ተመራማሪዎች ከመሬት ጋር ተመሳሳይነት ያላት እና ለመኖር ምቹ ልትሆን የምትችል አዲስ ፕላኔት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

መጠነ ግዝፈቷ ከምድር ጋር ሲነፃፀር በ6 በመቶ ብቻ የምትልቀው ይህች ፕላኔት፤ ከመሬት 146 የብርሀን ዓመት ርቃ እንደምትገኝ ተነግሯል።

“HD 137010 b” የሚል ስያሜ ያገኘችው ፕላኔቷ ኮከቧን ለመዞር 355 ቀናት የሚፈጅባት ሲሆን፤ ይህም ከምድር ዓመታዊ ዑደት ጋር እጅግ የተቀራረበ እንደሆነ ተገልጿል።
January 29, 2026 at 2:15 PM
ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ውጪ የባንክ ሥራ በመስራት ኢትዮጵያ ከ14 ሚሊየን ዶላር በላይ እንድታጣ በማድረግ የተጠረጠረችው ቻይናዊት ግለሰብ ክስ ተመሰረተባት፡፡

ሊንግ ቹንግ የተባለችው ተከሳሽ በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ ሰዎች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሲፈልጉ በእነዚያ ሀገራት ከሚገኙ ያልተያዙ ግብረ አበሮቿ ጋር ገንዘቡን በመሰብሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ 10 ግለሰቦች ሲያስተላልፉ መቆየታቸው በክሱ ላይ ተመላክቷል፡፡
January 29, 2026 at 2:14 PM
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች በልማት ዕቅዶች ውስጥ እንዲካተቱና በስርዓት እንዲመሩ ስትራቴጂካዊ ተግባራት በትኩረት እየተሰሩ ነው አለ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር።

ሚኒስቴሩ በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ የተሰሩ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸ በአርባምንጭ ከተማ እየገመገመ ነው

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የአካባቢ ጥበቃን የህልውና ጉዳይ አድርጋ እየሰራች ነው
January 29, 2026 at 2:13 PM
በምርጫ ብቻ፡ የሉዓላዊነታችንና የሰላማችን መተማመኛ!

በኢትዮጵያችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመክፈትና የዴሞክራሲ ሥርዓትን በፅኑ መሰረት ላይ ለመትከል "በምርጫ ብቻ" የሚለው መርህ ብቸኛው የሰላማዊ ስልጣን ሽግግር መንገድ ነው።

ይህ መርህ የዜጎችን ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥና የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሕዝብ ድምፅ ለመወሰን የሚያስችል ታላቅ የድል ጎዳና ነው።
January 29, 2026 at 2:08 PM
#ሪፖርታዥ

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሀገሪቱን ምርት (GDP) እስከ 12 በመቶ እንዲያግዝ እየተሰራ ነው:- የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ፖሊሲ አርቅቃ ሲትተገብር ቆይታለች፤ ከእነዚህም አንዱ ላለፉት 5 ዓመታት ሲሰራበት ቆይተው ታህሳስ 2018 የተጠናቀቀው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ነው።
January 29, 2026 at 2:06 PM
ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት፡ የግንባ አጋሬ ወጣቶች የድል ጉዞ

“እኛ ወጣቶች በአንድ ልብ ስንሠራና በአንድ ድምፅ ስንናገር ለውጥ መፍጠር እንችላለን። ጽናታችንን አጠናክረን፣ ማኅበራችንን የለውጥ ተምሳሌት እናደርጋለን!”

ይህ የወጣቶቹ የጋራ መፈክር ነው። በአመያ ዙሪያ ወረዳ፣ ግንባ አጋሬ ቀበሌ የሚገኘው “ኦትድ ፓፃና ቡና አምራች ማኅበር” አባላት ዛሬ ላይ ቆመው የትናንቱን ፈተና በድል ይተርካሉ።
January 29, 2026 at 2:04 PM
የእዉነት ዘበኞች እና የዲጂታል ዘመን ግንባር ቀደም መሪዎች መሆን አለብን:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም ጋር በመተባበር "ኮሙኒኬሽን በድጂታል ዘመን:-ከፈጠራ እስከ ውጤት"በሚል መሪ ቃል ለክልል፣ዞን ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
January 29, 2026 at 2:01 PM
ምርጫ 2013 የዴሞክራሲ ምህዳር ፋና ወጊ

ኢትዮጵያ በለዉጥ ማግስት በ2013 ዓ.ም ያደረገችዉ ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ታሪክ የተሻለ የዴሞክራሲ ምህዳር የታየበት ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ ያኔ ምርጫ ስታካሂድ ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታ፣ የኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት፤ የጋዛ ጦርነት፣ የውጭ የዲፕሎማሲ ጫናና ሌሎችም የውጫዊ ጫናዎች የነበሩበት ወቅት ነዉ፡፡
January 29, 2026 at 2:00 PM
የቱሪዝም እመርታ በክልላችን፦ ከሀላላ ኬላ_ዝሆን ዳና እስከ ደንቢ ሎጂ የሰመረዉ የብልፅግና ራዕይ

በመደመር ዕሳቤ የሚመራዉ የመደመር መንግስት በኢትዮጵያ ተዘንግተው የቆዩ የተፈጥሮና የታሪክ ፀጋዎቿን ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ምንጭነት ለመቀየር በጀመረችው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ፣ በክልላችን የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ማራኪ ሳቢና ትዉልድ ተሻጋሪ አሻራዎች ናቸዉ።
January 29, 2026 at 1:58 PM
በክልሉ በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ የሚፈጸም የተፋሰስ ልማት ስራ በሁሉም ዞኖች በይፋ ተጀመረ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዘንድሮ በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በክልሉ 1ሺህ 200 መቶ ነባርና አዲስ ንዑሳን ተፋሰሶች 2 መቶ 72 ሺህ ሄክታር መሬት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን በሚቀጥሉት 45 ቀናት ወደ ስራ የተገባ መሆኑ ተገልጿል፡፡
January 28, 2026 at 9:26 AM
የካፋ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል::

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው ያለፈውን 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 25ኛውን ጉባኤ ቃለጉባኤ መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ነው የጀመረው::

በመቀጠል ምክር ቤቱ የዞኑን ዋና አፈ ጉባኤ ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በዚህም ክብርት ወ/ሮ አሚናት ሀሰን የካፋ ዞን ዋና አፈጉባኤ እንዲሆኑ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቀረበውን የሹመት ፕሮፖዛል ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤ ተጀምሯል::
January 28, 2026 at 9:24 AM
የተፋሰስ ልማት ሥራ ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በተጓዳኝ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የጎላ ፋይዳ አለው - አቶ ማስረሻ በላቸው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የ2018 ዓ/ም የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ የተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ መኒት ጎልዲያ ወረዳ እየተካሄደ ይገኛል

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፥ በክልሉ ከዚህ ቀደም በተከናወነው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ውጤት ተመዝግቧል
January 28, 2026 at 9:23 AM
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የ2018 ዓ/ም የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ የተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት በምዕራብ ኦሞ ዞን፣መኤኒት ጎልዲያ ወረዳ እየተካሄደ ነዉ

በክልሉ እየተከሰተ ያለዉን የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የመሬት፣ የውሃና የሰው ሀብት መጠበቅ፣ ማልማትና በላቀ ደረጃ በማቀናጀት ጥቅም ላይማዋል ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መኾኑ ነዉ
January 28, 2026 at 9:21 AM
ከተማን ከቀበሌ የሚያገናኘው መንገድ በመገንባቱ በአካባቢያቸው ይታይ የነበረውን የመንገድ ችግር እንደፈታላቸው በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ ሾታ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በኢሳራ ‎ወረዳ የመንገድ ትስስር የምግብ ዋስትና ፕሮግራም (RCFSP) ከ2017 ዓም መጨረሻ ጀመሮ ከባሌ - መነሳ 16ኪሜ የመንገድ ጥገና፣1 የስትራክቼር እና ባሌ _ሾታ 12.37ኪሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
January 27, 2026 at 6:26 AM
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ እየተሰሩ ያሉ አምስት ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ ክልል ቢሮ የህንጻ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፥ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ተቋርጩ በሙሉ አቅም ሥራውን እንዲያፋጥን አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
January 27, 2026 at 6:25 AM
የሚዛን አማን ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አሁን ያለውን የህዝብ ቁጥር የሚሸከም ሊሆን ይገባል"ቋሚ ኮሚቴው

በቤንች ሸኮ ዞን የሚዘን አማን ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በፍጥነት እያደገ ካለው የህዝብ ቁጥርና የከተማው መስፋፋት ጋር በሚጣጣም በልኩ መሻሻል እንዳለበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰቧል።
January 27, 2026 at 6:23 AM
ሪፖርታዥ‎

በክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመሆኑ የክልሉን የወጭ ፍላጎት በገቢ ለመሸፈን ታልሞ እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ህይወት አሰግድ ገለፁ።

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ8 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ነው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ህይወት አሰግድ የገለፁት።

January 26, 2026 at 1:49 PM
መንግሥት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በማዘመንና ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተግባራዊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን የምትመክትበት አዲስ አቅም ገንብታለች ያሉት አፈ ጉባዔው፤ የጤና ሥርዓታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ እየዘመነ ነው ብለዋል

አፈ ጉባዔው ይህንን ያሉት የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ከኢትዮጵያ መጥፋቱን ተከትሎ ዛሬ በተዘጋጀው የማብሰሪያ መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው
January 26, 2026 at 1:47 PM
ማርበርግ ቫይረስ ሊያደርስ የነበረውን አስከፊ ጉዳት በተቀናጀና ጠንካራ የበሽታ መከላከል ሥርዓት መቆጣጠር መቻሉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ

ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከል በወሰደችው የተቀናጀና አስቸኳይ ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓት ቫይረሱን ማጥፋት ችላለች

በዚህምኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና አደጋን በመከላከል በጥቅምት ወር ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስን ከወራት በኋላ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት መቻሏን ተከትሎ የዕውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል
January 26, 2026 at 1:46 PM
ኢትዮጵያ ለጀመረችው አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሽግግር አስተማማኝና ተመጣጣኝ የኃይል አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) ገለፁ።

የቻይና ሳውዘርን ፓወር ግሪድ ቴክኖሎጂ እና የኤዳን ኤሌክትሮ ፓወር ግሩፕ ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ዓላማን የሰነቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መስርተዋል።
January 26, 2026 at 1:45 PM
በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል አለ የጤና ሚኒስቴር፡፡

የኢትዮጵያ ድንገተኛ የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ፈጣን ምላሽና አመራር ስኬቶች እንዲሁም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቁጥጥር ማብሰሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ አጋር አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
January 26, 2026 at 8:06 AM
በታርጫ ከተማ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ፡ የ67 ሚሊዮኑ ኮከብ ነዳጅ ማደያ ተመረቀ

በዳውሮ ዞን በታርጫ ከተማ የንግድ እንቅስቃሴና የትራንስፖርት ፍሰት ላይ ተጨማሪ ዕድል ተፈጥሯል። ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለተጓዦች የነዳጅ እጥረት ስጋት ሆኖ ቢቆይም፣ ዛሬ ግን ያ ስጋት የሚቀንስ ኢንቨስትመት ወደ ሥራ ገብቷል።

በ67 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ በከተማዋ ሁለተኛው ሲሆን፣ ከግንባታ እስከ አቅርቦት ድረስ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈስሶበታል።
January 25, 2026 at 3:52 PM
እንኳን ለ"ከይ ቢያርግ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምድር፣ በምዕራብ ኦሞ ዞን አረንጓዴ ተፈጥሮ መሃል፣ አንድ ብሄረሰብ አዲሱን ዓመት ለመቀበል ደጃፉን ከፍቷል

የጥንታዊ እሴቶች ባለቤት የሆነው የዲዚ ብሔረሰብ አሮጌውን ዘመን በይቅርታ ሸኝቶ፣ አዲሱን በበረከት የሚቀበልበት "ከይ ቢያርግ" የዘመን መለወጫ በዓል ደርሷል

"ከይ ቢያርግ"ምንድን ነው?

"ከይ ቢያርግ" ለዲዚ ብሔረሰብ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የምርት በረከትና የባህል መገለጫ ቀን ነዉ
January 25, 2026 at 3:50 PM