Southwest Communications
swc79.bsky.social
Southwest Communications
@swc79.bsky.social
We are delivering you an update and reliable information about Southwest Ethiopia Peoples Regional state activities, news, and national & international issues
ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ ሥራ የመጀመሪያው መዳረሻ የሆነው እና በ36.7 ሄክታር የጥብቅ ደን እና የተፈጥሮ ኃብት ስጦታ የተዘረጋው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል።

ኢኮ ሎጁ የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት አመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ኃብትን እና ለዘመናት የሚዘልቅ አለምአቀፍ ደረጃን የመጠበቅ እድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው።
January 19, 2026 at 9:23 AM
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ እንዳሉት፥ በክልሉ የሚሰበሰበውን ገቡ ለማሳደግ ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት በተከታታይነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

እነዚህ ስራዎች ለገቢው ማደግ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ክልሉ ካለው ገቢን የማመንጨት አቅም አንፃር አሁንም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል
January 17, 2026 at 12:55 PM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የገጠር ኮሪደር የአርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት በመለወጥ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሀገራዊ ሥራ ነው።

ዛሬ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የተሰሩትን የሞዴል ገጠር ኮሪደር ስፍራ ጎብኝተናል። ሞዴል ሥራው እያንዳንዳቸው ሳሎን፣ መኝታ ቤቶች፣ የእንስሳት ክፍል እና የውጭ መጸዳጃ ክፍሎች ያላቸው አስር ዘመናዊ ቤቶችን ያካተተ ነው።
January 17, 2026 at 12:54 PM
ገበታ ለሀገር በመጀመሪያ ዙር ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወንጪን፤ ከምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ እና ኮንታ ዞንን የሸፈነውን ኮይሻን፣ ከአማራ ክልል የጣናን ምዕራባዊ ዳርቻ የተንተራሰችውን ጎርጎራን አካትቷል። ሦስቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሰፊ ቦታ የሚሸፍኑ፣ በርካታ አማራጮችን የያዙ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ናቸው።

የመደመር መንግሥት - ገፅ 269
January 17, 2026 at 12:53 PM
የገበታ ቱሪዝም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመሩ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ በመሰረታዊነት እየቀየሩ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ ከአንድ ድንጋይ ከተጠረቡ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጀምሮ እስከ ጥያ ትክል ድንጋይ፣ ከሶፍ ዑመር ዋሻ እስከ ጎንደር አብያተ መንግስታት፣ ከአክሱም ሐውልት እስከ ሐረር ግንብ በርካታ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ባለቤት ናት።
January 17, 2026 at 12:52 PM
"ቲኬሻ ቤንጊ" የሸኮ ብሄር የዘመን መለወጫና የምሰጋና በዓል በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር አዳራሽ እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የብሄሩ ተወላጆች፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች እየታደሙ ነው
ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
January 17, 2026 at 9:53 AM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል።

ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን ያገለግላል።
January 17, 2026 at 9:50 AM
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን አዲስ ከተሰራው እና በመጠናቀቅ ላይ ከሚገኘው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።

#PMOEthiopia
January 17, 2026 at 6:32 AM
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣በአንጋፋውና ተወዳጁ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈተ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ፤ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በኪነ-ጥበብና በመዝናኛ ዘርፍ ካበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ባሻገር፣ አገርና ሕዝብን የሚወድ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎችም የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በስፋት ያስተዋወቀ ባለሙያ እንደነበር ገልጸዋል።
January 16, 2026 at 2:44 PM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል። ነጻነት በተለይም በሕዳሴ ግድብ በተዘጋጀው የ2016 አዲስ ዓመት የመቀበያ ፕሮግራም የነበረውን አስተዋጽዖ ሁሌም አስታውሰዋለሁ። ሁላችንም አዲሱን ዓመት በደስታ እንድንቀበል አድርጎን ነበር። ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እመኛለሁ።"
January 16, 2026 at 2:41 PM
ምጥን መኖ በጥራትና በብዛት በማዘጋጀት የራሳችንን ገቢ ከማሳደግ ባለፈ ገበያውን ለማረጋጋት በቂ ግንዛቤ ወስደናል ሲሉ ሠልጣኞች ተናገሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ እንስሳትና ዓሳ ሀበት ልማት ዘርፍ ከክልሉ FSRP እና ግብርና ሚንስትር ጋር በመተባበር በምጥን መኖ ዝግጅት ለተደራጁ ወጣቶችና ባለድርሻ አካላት በተግባር የታገዘ የአሠልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።
January 16, 2026 at 1:39 PM
ብልጽግና ፓርቲ በየዘርፉ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ተግባራት እንደሚያጠናክር የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ።

በሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የቆየው የፓርቲው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም መድረክ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ገበያን ለማረጋጋት የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም ተጠናቋል፡፡
January 16, 2026 at 1:37 PM
በኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት የተሠሩ ሥራዎች ጤናማ ትውልድ ለማፍራት የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው በዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች ገለጹ።

የኢትዮጵያ የሕጻናት ሄማቶሎጂና ኦንኮሎጂ ማኅበር የምሥረታ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ጤናን ለመጠበቅ፣ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
January 16, 2026 at 1:36 PM
በፕሮግራሙ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅና የታዩ ጉድለቶችን ለማረም የአፈጻጸም ግምገማ ማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑ ተመላከተ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሰት ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ (FSRP) የ2018 ዓ/ም የግማሽ ዓመት የዕቅደ አፈጻጸም ግምገማ በሚዛን አማን እያካሄደ ይገኛል።
January 16, 2026 at 1:35 PM
መጪውን የኢትዮጵያ ብልጽግና ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፏን እያዘመነች ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል ሀሳብ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም የሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ የሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
January 16, 2026 at 1:34 PM
በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ጋዳ ጋሪ ቀበሌ በ8.5 ሄ/ር ማሳ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የበጋ መስኖ ስንዴ አሁናዊ ገፅታ በፎቶ

የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
January 15, 2026 at 1:49 PM
የፋይናንስ እምርታ በኢትዮጽያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል በተሰናዳው እና ስድስት የሀገራችንን የፋይናንስ እና የገቢ ሥርዓት በመምራት ላይ ያሉ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም በሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ በሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል

ኢትዮጵያ ባለፉት 5 አመታት በፋይናንስ አካታችነት ተጨባጭ እድገት ያስገኙ ሰፊ መዳረሻ ያላቸው የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርሞች አካሂዳለች
January 15, 2026 at 1:48 PM
ኢብራሂም ተማም

በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት የተገልጋይ እርካታን ለማረጋገጥና የሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ገለጹ።

በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም በመጀመሪያ ዙር ወደ ተግባር ለሚገቡ የጤና ቢሮ እንዲሁም የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በታርጫ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
January 15, 2026 at 1:46 PM
በመኧን ብሔረሰብ "ዴጊያ"የተሰኘ ትውፊታዊ ቲያትር ተመረቀ

በመርሃ ግብሩ ላይ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንዳሉት፣በዞኑ ካሉት ባህላዊ እሴቶች መካከል በመኧን ብሔረሰብ ዘንድ ጥላቻን በማፍረስ እርቀ ሰላም ለማውረድ የሚረዳውን ባህላዊ እሴት መሠረት በማድረግ የተሰራው ቲውፈታዊ ትያትር እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
January 15, 2026 at 1:45 PM
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ አቶ አደም ፋራህ÷ እንደ ገዥ ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን እና ያለፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
January 15, 2026 at 1:43 PM
የፕሮግራም በጀትን ከታቀዱ ግቦች አንጻር በመጠቀምና ዕቅድንና ከበጀት ጋር በማስተሳሰር የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በፕሮግራም በጀት አሠራርና አተገባበር ላይ ለክልል ቢሮ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተሮች/ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና በሚዛን አማን እየሰጠ ይገኛል።
January 15, 2026 at 8:49 AM
ዴጊያ"የተሰኘ ትውፊታዊ ቲያትር ከደቂቃዎች በኋላ ይመረቃል።

በመኧን ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የሰላም ግንባታ ላይ ያተኮረ "ዴጊያ"የተሰኘ ትውፊታዊ ቲያትር ከደቂቃዎች በኋላ ይመረቃል።

በመኧን ብሔረሰብ የግጭት አፈታትና የሰላም ግንባታ ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ትውፊታዊ ቲያትር ነው ።

በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ የሚከናወነው የምረቃ መርሐ ግብር ከደቂቃች በኋላ የሚጀመር ይሆናል።

በምረቃ መረሐ-ግብሩ የክልል፣የዞን አመራሮችና ሌሎችም እየተሳተፋ ነዉ።
January 15, 2026 at 8:46 AM
በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የተጀመረውን የእንስሳት ተዋጽኦ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መኖ ማቀነባበሪያ እንዱስትሪዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ እንስሳትና ዓሳ ሀበት ልማት ዘርፍ ከክልሉ FSRP እና ግብርና ሚንስትር ጋር በመተባበር በምጥን መኖ ዝግጅት ለተደራጁ ወጣቶች፣ ለባለሙያዎችና አመራሮች የአሠልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነው።
January 15, 2026 at 8:44 AM
የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ለፌደራል ስርዓቱ መረጋገጥ ከፍ ያለ ሚና አለው -አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተከበረው 20ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና መርሐ-ግብርና አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በዓሉ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የእርስ በእርስ ትውውቅ እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል
January 15, 2026 at 8:43 AM
#የመደመር_ተስፋ

ማንኛውም መንግሥት ሀገሩን የመለወጥ ርዕይ ከሌለው ለእርሱ ባልተዘጋጀ የሌሎች ሕልም ሥር ይኖራል፡፡ ይህ ደግሞ ቅዠት እንጂ እውነት አመልካች ሕልም ሊሆን አይችልም፡፡ የለውጥ ጉዟችን ዓላማ ከእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ተላቅቆ በራሳችን ትልምና አእምሯዊ ፍኖት መጓዝ ነው። የራሳችን የሆነን የወደፊት መዳረሻችንን በራሳችን ዓይን መመልከት ነው። ራሳችን እናልማለን፤ ራሳችን እናያለን፤ ራሳችን እንተልማለን፤ ራሳችን እንጓዛለን፤ ከዚያም ራሳችን እንደርሳለን፡፡
January 15, 2026 at 7:20 AM