Fayda - Ethiopian National ID
banner
idethiopia.bsky.social
Fayda - Ethiopian National ID
@idethiopia.bsky.social
National ID Program office implementing inclusive digital ID in Ethiopia.
የመረጃ እድሳት በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን ለማረም ወይም መረጃ ለመለወጥ ቢያስፈልግ በቀላሉ ባሉበት ሆነው id.gov.et/update ላይ ገብተው ትክክለኛውን ቅደም ተከተል በመጠበቅ ማረም/መለዋጥ ወይም ደግሞ በአቅራቢያዎ በሚገኙ በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት በመሔድ የመረጃ ማዘመን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳመታወቂያ
November 20, 2025 at 8:21 AM
- የፋይናንስ አገልግሎቶች
- የተለያዩ መንግስት አገልግሎቶች
- የሰነድ ምዝገባ እና ማረጋገጥ አገልግሎት
- ከትምህርት ጋር ለተያያዙ አገልግሎቶች
- የትራንስፖርት እና መጓጓዣ አገልግሎቶች
- እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መልኩ ለማግኘት ያስችላል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ በዝርዝር ለመረዳት ድረገጻችንን id.gov.et/benefits ይጎብኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #FaydaID
September 23, 2025 at 10:13 AM
In commemoration of International Identity Day, team #Fayda stands empowered under the theme "My Identity My Umbrella".

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳለሁሉም #Inclusion #IDDAY2025 #myidentitymyumbrella
September 18, 2025 at 9:33 AM
In Ethiopia, identity is more than just a card — it is dignity, protection, and opportunity. Through the #Fayda ecosystem, we are building a trusted digital foundation where everyone in #Ethiopia stands under one umbrella.

My Identity, My Umbrella.

#IDDAY #identityday #IdentityMatters
September 15, 2025 at 12:51 PM
እንኳን 1500ኛው የነቢዩ መሐመድ መውሊድ (ልደት) አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መታወቅ ለመተማመን!

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳለሁሉም #መውሊድ
September 3, 2025 at 3:08 PM
የፋይዳ ቁጥር ጠፍቶብዎታል? መረጃ ማስተካከል ፈልገዋል? ወይስ የፋይዳ ካርድ ህትመት ማዘዝ?

በቀላሉ የፋይዳ ቴሌግራም ቦት FaydaHelpBot በመግባት የሚፈልጉትን አገልግሎት ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅለመተማመን #DigitalID #Fayda
August 26, 2025 at 3:30 PM
መረጃ ቢያስተካከሉ ወይም ቢለወጡ የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎ ግን እንደማይቀየር ያውቃሉ?

በፋይዳ ምዝገባ ወቅት ያስገቡት የግል መረጃ ላይ ማስተካከያ ቢያደርጉ የፋይዳ መረጃዎን አዘመኑ እንጂ የፋይዳ ቁጥርዎ ግን ያው ነው ፤ አይቀየርም።

የመረጃ ለውጥ በሚያመለክቱበት ጊዜ በስልክ እና በኢሜል የሚላክልዎ ባለ 29 አኃዝ የመከታተያ ቁጥር ሲሆን ፤ ጥያቄዎ ተስተካክሎ ሳይላክ ከቆየ ያለበትን ሁኔታ ለመከታተል ይረዳል።

#ፋይዳመታወቂያ #ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም
August 8, 2025 at 2:08 PM
በምዝገባ ወቅት የተመዘገቡበትን የስልክ ቁጥር መለወጥ ወይም ማስተካከል ፈልገዋል?

1. በምዝገባ ወቅት የሌላ ሰው ስልክ ቁጥር አስገብተው አሁን ወደ ራስዎ ስልክ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ ድረገጻችን id.gov.et/update ላይ በመግባት መቀየር ይችላሉ።

2. እንዲሁም በምዝገባ ወቅት የራስዎ ስልክ ቁጥር ሲሞላ የቁጥር ስህተት ካጋጠመ id.gov.et/updatecenters ላይ በአቅራቢያ በሚያገኟቸው የመረጃ ማስተካከያ ጣቢያዎች በአካል በመሔድ መቀየር ይችላሉ።
August 2, 2025 at 5:24 PM
በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የፋይዳ ምዝገባ እና የመረጃ ማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረውና ኢምፔሪያል ፊት ለፊት በሚገኘው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በመሔድ የፋይዳ ምዝገባ እና በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን የማስተካከል አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #መሶብ #Fayda #MESOB
July 17, 2025 at 10:08 AM
ለወላጆች

ልጆችዎ ለፋይዳ ተመዝግበው ቁጥር አልደረሳቸውም ብለው አይጨነቁ ፤ በቀላሉ በስልክዎ ወደ *9779# በመደወል በራስዎ ማስላክ ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለተማሪ #መታወቅ #DigitalID
July 12, 2025 at 10:53 AM
በያዝነው የሰኔ ወር ባለው ከፍተኛ የምዝገባ መጠን መጨመር ምክንያት የፋይዳ ሲስተም አንድን ሰው በልዩ ሁኔታ ለማጣራት የሚወስድበት የጊዜ ልኬት በጥቂቱ ጨምሯል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ እስከ 4 ቀን ድረስ ሊቆይ ስለሚችል በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ የፋይዳ ቁጥር ካልደረሰዎ *9779# ወይም "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም
ፋይዳ ቁጥሩ እንዲላክ ማድረግ ይችላሉ።
July 3, 2025 at 9:17 AM
በየትኛው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አማራጭ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ያውቃሉ?
July 3, 2025 at 7:53 AM
People need to understand that this digital ID is foundational for the digital economy." National ID Program's Executive Director, Yodahe Zemichael, in his interview with Biometric Update,

Read the full interview: www.biometricupdate.com/202506/ethio....

#FaydaID #DigitalID #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ
June 25, 2025 at 9:02 AM
በመድረኩም ተቋማቶቹ ለቅንጅቱ የሚያስፈልጉ የስርዓት ለስርዓት ትስስር መደላድሎች ለመፍጠር የሚያስችሏችውን ነጥቦች የለዩ ሲሆን በቀጣይ በሚሠሩ ሥራዎች ላይ በመወያየት እና በዝርዝር በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID
June 13, 2025 at 9:39 AM
The Nation ID Program is looking for a Construction Supervision Consultant to lead and oversee our exciting office renovation and furniture installation projects.

Details to Apply: projects.worldbank.org/en/projects-...
June 10, 2025 at 5:51 PM
From insight to impact – paving the digital path for 90 million Ethiopian citizens. We are proud to share our very first self-assessment report, developed in partnership with Digital Impact Alliance, ahead of #ID4Africa2025.

Report: id.et/documents
May 19, 2025 at 8:42 AM
ያስተውሉ
ለከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መደረጉን ተከትሎ ተማሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አስፈላጊ የፋይዳ አገልግሎቶች፡

1. የፋይዳ ቁጥር ከጠፋባችሁ/ ካልደረሳችሁ *9779# መደወል
2. በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን ለማደስ id.gov.et/update ላይ በመግባት ወይም የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ላይ በቀላሉ ማደስ

3. በተጨማሪ ለማንኛውም ጥያቄ t.me/+RJ5TcWZ_HvU... የቴሌግራም ግሩፕ ይቀላቀሉ
May 13, 2025 at 8:06 AM
የፋይዳ ለኢትዮጵያ ሩጫ የፊታችን እሁድ ይካሔዳል።

ከ20,000 በላይ ተሳታፊዎች የሚኖረው የ5 ኪ.ሜ የፋይዳ ሩጫ ግንቦት 3፣2017 እንደሚካሄድ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሙሉ መግለጫዉን : id.gov.et ላይ ያገኙታል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳሩጫ #DigitalID
May 6, 2025 at 11:52 AM
ዝግጁ ነዎት?

የፊታችን እሁድ ግንቦት 3 የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በመዲናችን ለሚያካሔደው የፋይዳ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

በነጻ የሩጫ ቲሸርት ለመሸለም የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከታተሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳሩጫ #DigitalID
May 5, 2025 at 8:51 AM
የውይይት ጥሪ

ረቡዕ ሚያዝያ 29 ቀን ከቀኑ 8:30 - 10:30 ሰዓት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ የሚደረገው የኦንላይን ውይይት መድረክ ላይ በዚህ ሊንክ zoom.us/j/9202514319... በመግባት ይሳተፉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳመታወቂያ #DigitalID
April 29, 2025 at 12:36 PM
The new Mesob platform — inaugurated by PM Abiy Ahmed — brings 41 services from 12 agencies into one place for faster, more transparent service. Fayda Digital ID is being integrated into all Mesob services. Read More: id.gov.et/news

#faydaforservices #ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለአገልግሎት
April 28, 2025 at 12:06 PM
በፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ " Fayda ID" ምን አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር play.google.com/store/apps/d... እንዲሁም ከአፕ ስቶር apps.apple.com/app/fayda-id... ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ፣ የፋይዳ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID #InclusiveID
April 23, 2025 at 1:10 PM
የመረጃ ስህተት እንዴት ማስተካከል ይቻላል?

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #መታወቅ
April 18, 2025 at 6:41 AM
ፋይዳን ለትምህርት ቤት ምዝገባ

ለመጪው የትምህርት ዘመን በመንግስትም ሆነ በግል የትምርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደም ሁኔታ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ወላጆች ከ 5 አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ተማሪዎችን ከወዲሁ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡

የፋይዳ ቁጥር ከጣፋብዎ ወይም ካልደረስዎ *9779# ይደውሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለተማሪ #መታወቅ #DigitalID
April 11, 2025 at 6:22 AM
ለፋይዳ ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ ሲስተሙ ማንነትን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የሚወስድበትን ጊዜ በማስረዘም ልዩ ቁጥርዎ በጊዜው እንዳይደርስዎ ያደርጋል። የፅሁፍ መልዕክት ካልደረሰዎ ወይም ከጠፋብዎ *9779# ላይ ጥሪ በማድረግ ወይም የፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ "Fayda ID" በመጠቀም ወደ ስልክዎ ይላኩ። መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር play.google.com/store/apps/det… ወይም ከአፕ ስቶ½� apps.apple.com/app/fayda-id/iï¿/i… ያውርዱ።
April 8, 2025 at 1:13 PM