Ethiopique - ኢትዮጲክ
banner
ethiopique202.bsky.social
Ethiopique - ኢትዮጲክ
@ethiopique202.bsky.social
Local news and resources for Amharic speaking immigrant communities in DC-MD-VA. Web: www.ethiopique.com
ባሳለፍነው ሰሞን ኦክቶበ 8 ከጧቱ 10፡24 ላይ አንዲት የ27 አመት ወጣት በኤ አይ በተፈጠረ ምስል በመጠቀም ለባለቤቷ አንድ ሰው ገፍትሯት ቤታቸው እንደገባ በቴክስት ትነግረዋለች። ይህንን ተከትሎም ባልየው ለፖሊስ በ911 ደውሎ ቤታቸው እየተዘረፈ እንደሆነ ይነግራቸዋል።
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾
ethiopique.com?p=7070
ከሰሞኑ የቲክቶክ ትሬንድ በነበረው ቪዲዮ ባሏን ፕራንክ ልታደርግ የሞከረች  አንዲት የሞንጎምሪ ካውንቲ ሴት ታሰረች
ባሳለፍነው ሰሞን ኦክቶበ 8 ከጧቱ 10፡24 ላይ አንዲት የ27 አመት ወጣት በኤ አይ በተፈጠረ ምስል በመጠቀም ለባለቤቷ አንድ ሰው ገፍትሯት ቤታቸው እንደገባ በቴክስት ትነግረዋለች። ይህንን ተከትሎም ባልየው ለፖሊስ በ911 ደውሎ ቤታቸው እየተዘረፈ እንደሆነ ይነግራቸዋል።  ፖሊሶችም ጉዳዩን ሊያጣሩ እንዲሁም ከተ…
ethiopique.com
October 17, 2025 at 8:16 PM
ስምዖን ጌታቸው የተባለ የ30 ዓመት ወጣት እሁድ ኦክቶበር 12 ምሽት በሳውዝ ኢስት ዋሽንግተን ዲሲ በጥይት ተመቶ መገደሉ ቤተሰቦቹንና ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመዶቹ ገዳዮቹ ወደፍትህ እንዲቀርቡና ፍርድ እንዲያገኙ እየጠየቁ ነው።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7064
የ30 ዓመቱ ስምዖን ጌታቸው በሳውዝ ኢስት ዲሲ በተተኮሰበት ጥይት ለህልፈት ተዳረገ። ወዳጅ ዘመዶቹ አግዙን ይላሉ
ስምዖን ጌታቸው የተባለ የ30 ዓመት ወጣት እሁድ ኦክቶበር 12 ምሽት በሳውዝ ኢስት  ዋሽንግተን ዲሲ በጥይት ተመቶ መገደሉ ቤተሰቦቹንና ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመዶቹ ገዳዮቹ ወደፍትህ እንዲቀርቡና ፍርድ እንዲያገኙ እየጠየቁ ነው። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀ…
ethiopique.com
October 17, 2025 at 4:00 AM
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS)፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው (ፎርም I-589) ሞልተው መልስ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች አመታዊ የጥገኝነት ክፍያ (Asylum Fee) እንዲከፍሉ የሚያዝ ደብዳቤዎችን መላክ ጀምሯል።
ዝርዝሩ
ethiopique.com?p=7059
ዩኤስሲአይኤስ አመታዊ የጥገኝነት አመልካቾች ክፍያ እንዲከፍሉ ለአመልካቾች ደብዳቤዎችን መላክ ጀመረ
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS)፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው (ፎርም I-589) ሞልተው መልስ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች አመታዊ የጥገኝነት ክፍያ (Asylum Fee) እንዲከፍሉ የሚያዝ ደብዳቤዎችን መላክ ጀምሯል። ጁላይ 4, 2025 በጸደቀው ቢግ ቢውቲፉል ቢል ላይ ከያዝነው የበጀት አ…
ethiopique.com
October 16, 2025 at 2:43 PM
... ያኔ ወላጆችን ሳይ እንዲሁም አንዳንዴ ደግሞ ትልልቅ ሰዎችም ሲገቡ እስር ቤት ውስጥ የባህል አለመግባባት ይኖራል እና በጣም ያሳዝኑኝ ነበረ ። አንዴ በጣም የማይረሳኝ፦ አንድ ሰውዬ የሽንት ችግር ነበራቸው። እና በጣም ሽንት ሲያስቸግራቸው፤ ሞል ውስጥ ከመኪናቸው ጎን ወደ ዳር ሆነው ሸኑ። ሲሸኑ ያዩአቸው ነጮች ደወሉባቸው እና ታስረው መጡ። ...
ዝርዝሩ ..👇🏾👇🏾
ethiopique.com?p=7051
ዶ/ር ሊሻን ካሳ የምስጋና ምሽት ተዘጋጀላቸው
የኢትዮጲክ ባልደረቦች ከሰሞኑ ከቀድሞዋ የሞንጎምሪ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ የኢስት ካውንቲ ዳይሬክተር ከነበረችው ዶክተር ሀምራዊት ግብዣ ይደርሳቸዋል፡፡ ይህ ግብዣ ደግሞ ለበርካቶች አገልግሎትን የሰጠችውን ዶክተር ሊሻን ካሳን ለማመስገንና ዕውቅና ለመስጠት የተደረገ ፕሮግራም ላይ እንድንገኝ የሚጋብዝ መልዕክት ነበር፡፡ ታ…
ethiopique.com
October 15, 2025 at 5:53 PM
እንደ ባልቲሞር ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪዎቹን የ32 ዓመቱ ኤፍሬም መለክቴ እና የ67 ዓመቷ ፋሲካ ጻዲቅ መሆናቸውን ይፋ ቢያደርግም፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በርካታ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ አሉ።
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾
ethiopique.com?p=7031
የአቶ መኮንን ገዳይ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በኒውዮርክ መያዛቸው ታወቀ፤ በተጠርጣሪዎቹና በሟች መካከል ስለነበረው ግንኙነትና የግድያው መንስኤ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል
ባሳለፍነው ሰሞን ባጋራናችሁ ዜና የባልቲሞር ነዋሪ የነበሩት የ71 አመቱ አዛውንት አቶ መኮንን ሀብተስላሴ ሴፕቴምበር 25 ቀን በምስራቅ ባልቲሞር በ1200 ብሎክ የኖርዝ ፓተርሰን ፓርክ አቬኑ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተገለው እንደተገኙና ፖሊስም ገዳዮችን ለመያዝ ምርመራ እያደረገ እንደነበር ይታወቃል። ፖሊስ ታ…
ethiopique.com
October 14, 2025 at 8:48 PM
በሎርተን ከተማ በተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ ምክንያት በአንድ ማይል ራዲየስ ያሉ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ አስጠነቀቀ
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7043
October 14, 2025 at 8:47 PM
በአብቹ ለማ

የፌዴራል መንግስት ከተዘጋ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል። ቀኑ በተራዘመ ቁጥር በሠራተኞች፣ በቤተሰቦቻቸውና በአገልግሎት ሰጪ ቢዝነሶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ከዚህ አንፃር በቨርጂኒያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል መለስተኛ ቅኝት አድርገናል።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7026
የፌዴራል መንግስት መዘጋት በቨርጂኒያ የሚኖሩ የፌዴራል ሠራተኞችና ቢዝነሶች ላይ ያስከተለው ተፅዕኖ
በአብቹ ለማ  የፌዴራል መንግስት ከተዘጋ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል። ቀኑ በተራዘመ ቁጥር በሠራተኞች፣ በቤተሰቦቻቸውና በአገልግሎት ሰጪ ቢዝነሶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ከዚህ አንፃር በቨርጂኒያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል መለስተኛ ቅኝት አድርገናል።   በቨርጂኒያ የሚገኙ የፌዴራል…
ethiopique.com
October 12, 2025 at 7:37 PM
የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት መዘጋቱ በዚሁ ከቀጠለምና ወደ ኖቨምበር ከተሻገረ የፉድ ስታምፕ ተጠቃሚዎችን የድጎማ ገንዘብ ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ስለማይኖር ስቴቶች ለፉድ ስታምፕ ደንበኞች ገንዘብ እንዳይልኩ አስጠነቀቀ።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7020
የመንግስት በጀት በኮንግረስ ካልተፈቀደ ስቴቶች ፉድ ስታምፕ እንዳይሰጡ ታዘዘ
የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት መዘጋቱ በዚሁ ከቀጠለምና ወደ ኖቨምበር ከተሻገረ የፉድ ስታምፕ ተጠቃሚዎችን የድጎማ ገንዘብ ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ስለማይኖር ስቴቶች ከኖቨምበር ጀምሮ ለፉድ ስታምፕ ደንበኞች ገንዘብ እንዳይልኩ አስጠነቀቀ። ይህ ማስጠንቀቂያ ከኮቪድ ወረርሺኝ በኋላ በተለይም የምግብ ዋስትና እ…
ethiopique.com
October 11, 2025 at 3:34 PM
የፌደራል መንግስት አስረኛ ቀኑን ይዞ በቀጠለው የመንግስት መዘጋት ወቅት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ሰራተኞችን በቋሚነት ከስራ የማሰናበት ደብዳቤዎችን (ኢሜይሎችን) መላክ ጀምሯል። ዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 10 የፌደራል መንግስቱ የበጀትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ረሰል ቮውት በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ “የአር.አይ.ኤፍ (RIF) ርምጃ ተጀምሯል” ሲሉ አስታውቀዋል።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7017
አስረኛ ቀኑን የያዘውን የመንግስት መዘጋት ተከትሎ የፌደራል መንግስት ለበርካታ ሰራተኞች ከስራ ማሰናበቻ ደብዳቤዎችን ላከ
የፌደራል መንግስት አስረኛ ቀኑን ይዞ በቀጠለው የመንግስት መዘጋት ወቅት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ሰራተኞችን በቋሚነት ከስራ የማሰናበት ደብዳቤዎችን (ኢሜይሎችን) መላክ ጀምሯል። ዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 10 የፌደራል መንግስቱ የበጀትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ረሰል ቮውት በኤክ…
ethiopique.com
October 10, 2025 at 11:09 PM
የዲስትሪክቱ የቅጥር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (Department of For-Hire Vehicles ) በዩኒየን ስቴሽን ዙሪያ ስላሉ ህጎች ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ ደንቦቹ በከተማዋ ከሚገኙ በጣም በተጨናነቁ የትራንስፖርት ማዕከላት አንዱ በሆነው በዚህ ስፍራ የተሳፋሪዎችን፣ የአሽከርካሪዎችን እና የጎብኚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7013
ዲኤፍኤችቪ (DFHV) በዩኒየን ስቴሽን በራፍ ስለሚኖሩ ጥብቅ ደንቦች ለታክሲ አሽከርካሪዎች ማሳሰቢያ ሰጠ
የዲስትሪክቱ የቅጥር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (Department of For-Hire Vehicles ) በዩኒየን ስቴሽን ዙሪያ ስላሉ ህጎች ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ ደንቦቹ በከተማዋ ከሚገኙ በጣም በተጨናነቁ የትራንስፖርት ማዕከላት አንዱ በሆነው በዚህ ስፍራ የተሳፋ…
ethiopique.com
October 10, 2025 at 9:23 PM
አመታዊው የዩ ኤስ አርሚ የ10 ማይል ሩጫ ውድድርን በማስመልከት ዕሁድ ኦክቶበር 12 በዲሲ የሚገኙ በርካታ መንገዶች ላይ መኪና ማቆምም ሆነ ማሽከርከር እንደማይፈቀድ የዲሲ ፖሊስ አስታውቋል።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=7010
October 10, 2025 at 2:49 PM
የዩኤስሲአይኤስ (USCIS) ዳይሬክተር ጆሴፍ ኤድሎው የኢሚግሬሽን ማጭበርበርን እና የጥገኝነት (Asylum) ክምችትን ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነ አስታወቁ
ዝርሩ 👇🏾👇🏾

ethiopique.com?p=6981
የዩኤስሲአይኤስ (USCIS) ዳይሬክተር የኢሚግሬሽን ማጭበርበርን እና የጥገኝነት (Asylum) ክምችትን ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነ አስታወቁ
የአሜሪካ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (U.S. Citizenship and Immigration Services – USCIS) ዳይሬክተር የሆኑት ጆሴፍ ኤድሎው በቅርቡ ሴንተር ፎር ኢሚግሬሽን ስተዲስተዲስ (Center for Immigration Studies) ባዘጋጀው ውይይት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ዋና…
ethiopique.com
October 9, 2025 at 3:02 PM
በአብቹ ለማ
የዋሽንግተን ፖስት የኖቨምበር 2021 ዘገባ እና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፌቡራሪ 2025 የጥናት ውጤት በኖቨምበር 2/2021 በተካሄደው የቨርጂኒያ ምርጫ ዲሞክራቶችን ይደግፉ የነበሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሳይቀሩ የሪፐብሊካኖችን ተወካይ ግሌን ያንኪንን እንደመረጡ ያመላክታል። የዚህ ገፊ ምክያንት ደግሞ በወቅቱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተከተለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከኢትዮጵያውያንና…
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾

ethiopique.com?p=6975
በቨርጂኒያ 2025 የገቨርነሮች ምርጫ ኢትዮ-አሜሪካዊያን ማንን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል? የምርጫ መሥፈርቶቻቸውስ ምንድናቸው?
በአብቹ ለማ  የዋሽንግተን ፖስት የኖቨምበር 2021 ዘገባ እና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፌቡራሪ 2025 የጥናት ውጤት በኖቨምበር 2/2021 በተካሄደው የቨርጂኒያ ምርጫ ዲሞክራቶችን ይደግፉ የነበሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሳይቀሩ የሪፐብሊካኖችን ተወካይ ግሌን ያንኪንን እንደመረጡ ያመላክታል። የዚህ ገፊ ምክያንት…
ethiopique.com
October 8, 2025 at 2:35 PM
ማስታወቂያ
...
አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
October 7, 2025 at 3:34 PM
በአብቹ ለማ
የፌደራል መንግስት ከኦክቶበር 1/2025 እኩለ-ሌሊት ጀምሮ በከፊል መዘጋጀቱ ከታወቀ በኋላ የዲሲ ከንቲባ ብሎም የሜሪላንድና የቨርጂኒያ ገቨርነሮች የፌደራል ሠራተኞችን ለመደገፍ የተናጠልና የጋራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ጋር በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል።
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾

ethiopique.com?p=6977
October 7, 2025 at 2:02 PM
Yesterday we wrapped up our final Fishing with Ethiopique of 2025.

East Potomac Park was closed due to the shutdown, but we found a new spot and still had a great turnout.

Thank you to everyone who joined us this season; until we meet again when the weather gets warm.

#FishingWithEthiopique
October 5, 2025 at 3:00 PM
ማስታወቂያ
..

ማንኛውንም እቃ ወደ ኢትዮጵያ እንልካለን + እናመጣለን !

አድራሻ
3819C S George Mason Dr, Falls Church, VA 22041

ስልክ
571-579-1286 ወይም 571-579-0939

ዋሳ ኤክስፕረስ - የልብ አድርስ
October 3, 2025 at 6:06 PM
በዚህ ፕሮግራም ላይ ታዲያ የተለመዱትን ሽልማቶች ለአሸናፊ ልጆች ያዘጋጀን ሲሆን በዚህ ወር ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው አሸናፊዎችን የ50$ ጊፍት ካርድ ሳይሆን የ100$ ጊፍት ካርድ በ3 ዘርፍ ለሚያሸንፉ ታዳጊዎች (እድሜያቸው ከ15 ያነሱ) የምንሸልም ይሆናል።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=6966
October 3, 2025 at 4:11 PM
የአሌክሳንድርያ ፖሊስ የ62 ዓመት አዛውንት የሆኑትን አቶ ፍቅሬን አፋልጉኝ ብሏል።
ለመረጃው የዘወትር አንባቢያችንን አንተነህን dደመላሽን እናመሰግናለን።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=6904
September 30, 2025 at 10:53 PM
የዋይት ኃውስ በጀት ጽህፈት ቤት ኮንግረስ እ.ኤአ ከዛሬ ከመስከረም 30/2025 ቀነ-ገደብ በፊት በጀት ማፅደቅ ካልቻለ ተጨማሪ የፌዴራል ሰራተኞች ከሥራቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።
ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾

ethiopique.com?p=6903
September 30, 2025 at 2:27 PM
ማስታወቂያ
...
አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
September 29, 2025 at 7:32 PM
ማስታወቂያ . . .
ታዋቂዋ አርቲስት መክሊት ሀደሮ በመጪው ወር ኦክቶበር 18 2025 ላይ ከምሽቱ 8pm ጀምሮ ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የሞንጎምሪ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ ለ6 አመታት የለፋችበትን "ኤ ፒስ ኦፍ ኢንፊኒቲ" የተሰኘውን አልበም ታስመርቃለች።
በዚህ የአልበም ምርቃት ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ይህን ሊንክ ተጭነው የመግቢያ ትኬቱን ማግነት ይችላሉ።
bit.ly/meklith
September 27, 2025 at 12:43 PM
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ አዳዲስ ታሪፎችን ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ መድኃኒቶች፣ በከባድ መኪናዎች እና በቤት ፈርኒቸሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=6889
ፕሬዘደንት ትራምፕ ከኦክቶበር 1 ጀምሮ ወደ ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ እቃዎች ላይ አዲስ ታሪፍ ጣሉ
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ አዳዲስ ታሪፎችን ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ መድኃኒቶች፣ በከባድ መኪናዎች እና በቤት ፈርኒቸሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።  ይህ የቀረጥ ፕሮግራም በዋናነት የአገር ውስጥ ምርቶችን ለማሳደግና እንደሀገር በሌሎች አ…
ethiopique.com
September 27, 2025 at 12:26 AM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን በዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው።
ዝርዝሩ 👇🏾
ethiopique.com?p=6882
September 26, 2025 at 11:30 PM